በኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክ ርዕሰ አድባራት ዱባይ ሻርጃ አጅማን ሰአሊተ ምሕረት ቅድስት ማርያም ቤ/ክ ቤዛ ብዙኃን ሰ/ት/ቤት

Armenian Church Al Yarmook Sharjah, Sharjah, 1245
በኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክ ርዕሰ አድባራት ዱባይ ሻርጃ አጅማን ሰአሊተ ምሕረት ቅድስት ማርያም ቤ/ክ ቤዛ ብዙኃን ሰ/ት/ቤት በኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክ ርዕሰ አድባራት ዱባይ ሻርጃ አጅማን ሰአሊተ ምሕረት ቅድስት ማርያም ቤ/ክ ቤዛ ብዙኃን ሰ/ት/ቤት is one of the popular Religious Organization located in Armenian Church Al Yarmook Sharjah ,Sharjah listed under Church/religious organization in Sharjah , Religious Organization in Sharjah ,

Contact Details & Working Hours

More about በኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክ ርዕሰ አድባራት ዱባይ ሻርጃ አጅማን ሰአሊተ ምሕረት ቅድስት ማርያም ቤ/ክ ቤዛ ብዙኃን ሰ/ት/ቤት

+++የአህጉረ ስብከቱ መልዕክት+++
በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን።
“ኢንኅድግ ማኅበረነ- አንድነታችንን አንተው” ዕብ 10፥25

ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ ዕብራውያን ክርስቲያኖችን አንድነታቸውን እንዳይተው በአጽንዖት ያሳሰባቸው በአንድነት ውስጥ ተዘርዝረው የማያልቁ መንፈሳዊ እና ሥጋዊ በረከቶች ስላሉ ነው። አንድነት ሲኖር ሰዎች ባልንጀራቸውን ይወዳሉ። አንድነት ባለበት ቦታ ፍቅር እንጂ ጥላቻ ቦታ የለውም።የተወደዳችሁ ክርስቲያኖች ”ለፍቅር እንድንነቃቃ አንድነታችንን አንተው” ዕብ 10፥25 የተባለው ስለዚህ ነውና አንድነታችንን በፍቅር እንያዘው። በሌላ በኩል አንድነት ለመልካም ሥራ የሚቀሰቅስ፣ከክፉ ሥራ የሚያርቅ መለኮታዊ ስጦታ ነው። ሐዋርያው”ለመልካም ሥራ እንድንነቃቃ አንድነታችንን አንተው” ዕብ 10፥24 ማለቱ ሰዎች አድነታቸውን ሲያጸኑ በጎ ለማድረግ ይበረታሉና ነው። በዓለም ላይ ሰፍኖ የሚታየው ክፉ ሥራ ሰዎች በተለያዩ ምክንያቶች አንድነታቸውን ሲያጡ የተከሰቱ ናቸው። ስለዚህ አንድ ነን ከሚል የሰው ዘር ሁሉ መልካም ሥራ ይጠበቃል።
አንድነት ሰዎችን ልበ ሰፊና ይቅር ባይ ስለሚያደርጋቸው በወንድሞቻቸው ላይ ስሕተት ባዩ ጊዜ ይመክሯቸው ዘንድ ያበረታታቸዋል።ሰው እንደመሆናችን በሌሎች ልንበደል እና ሌሎችን ልንበድል እንችላለን።አንድነታችን ልባዊ ከሆነ ግን ይቅር ለማለት እና ይቅርታ ለመጠየቅ አንዘገይም። ውድ ልጆቻችን ከወንድሞቻችሁ ጋር ያላችሁ አንድነት ከወንድማችሁ በደል ይልቅ መብለጥ አለበት።ያን ጊዜ ሰውን በስሕተቱ መጉዳት ቀርቶ መምከርና በዓይነ ምሕረት ማየት ይቻላል። ንዋይ ኅሩይ ጳውሎስ አንድነት መተራረምን፣መመካከርን የሚያመጣ መሆኑን ሲጽፍ እንዲህ ብሏልና “አንድነታችንን አንተው፤እርስ በእርሳችን እንመካከር እንጂ” ዕብ10፥25
ጠቢቡ ሰሎሞን ደግሞ አንድነትን የመረዳዳት ምክንያት፤የተስፋ እናት፣የተድላ ሥጋ ወደብ እና የድል መሠረት ይላታል።አንድነትን አጥቶ ያለረዳት ከመቅረት፤ ተስፋን ከማጨለም፤ በሥጋዊ እና በመንፈሳዊ ተግዳሮት ድል ከመነሣት አንድነትን አጽንቶ ይዞ በተስፋ እና በድል መኖር ይሻላል። “አንድ ብቻ ከመሆን ሁለት መሆን ይሻላል።ቢወድቁ አንዱ ሁለተኛውን ያነሣዋልና፡አንዱ ብቻውን ሆኖ በወደቀ ጊዜ ግን የሚያነሳው ሁለተኛ የለውምና ወዮለት።ሁለቱም በአንድነት ቢተኙ ይሞቃቸዋል፡አንድ ብቻውን ግን እንዴት ይሞቀዋል? አንዱም አንዱን ቢያሸንፍ፡ሁለቱ በፊቱ ይቆማሉ፡በሦስትም የተገመደ ገመድ ፈጥኖ አይበጠስም” መጽ.መክ 4፥9-12
በረከታቸው ይደርብን እና ቅዱሳን ሐዋርያት እና የመጀመሪያዎቹ ክርስቲያኖች አንድ ልብ፡አንዲትም ነፍስ ነበራቸው የሐዋ.ሥራ 4፥32 በዚህ አንድነታቸው የተነሣ “በሕዝብ ሁሉ ፊት ሞገስ ነበራቸው” የሐዋ.ሥራ 2፥47 ፣ “ሕዝቡ ግን ያከብሩአቸው ነበር” ፤ “የሚያምኑትም ከፊት ይልቅ ለጌታ ይጨመሩለት ነበር” የሐዋ.ሥራ 5፥13-14 የተወደዳችሁ የመንፈስ ልጆቼ አንድነት ሞገስን፣ መከበርን፥መብዛትን እና መትረፍረፍን ይዞ እንደሚመጣ ተመልከቱ። አንድነትን ስንተው ክብርና ሞገሳችን ይሸሻል፤ በእኛም ላይ ክፉው ይሰለጥናል። ከሁሉም በላይ ቁጥራችን ይሳሳል። አንድነትቱን የሚያምን ሕዝብ ተከባብሮ ይከበራል፥ ይበዛል፣ይመላል እንጂ በቁጥር አይመነምንም። አንድነት ያለው አብሮ ይጸልያል።ያለ አንድነት የሚደረግ ጸሎት ቅድመ እግዚአብሔር ደርሶ ሥራ አይሠራም።አገልግሎታችን በአንድነት ሲከወን የሰዎችን አንድነት የሚወድ እግዚአብሔር ይባርከናል። አገልጋዩም የተመቸ የአገልግሎት ድባብ ስለሚያገኝ በሰቂለ ኅሊና በአንቃድዎ ልቡና ሆኖ ስለ ሕዝቡ ይጸልያል። ሊቀ ነቢያት ሙሴ የተገልጋዩ አንድነት ለእርሱ ለአገልጋዩ አገልግሎት መሥመር ወሳኝ መሆኑን ሲገልጽ እንዲህ አለ “ሕዝቡ ሁሉ አንድ አፍ ሆነው እግዚአብሔር ያለውን ሁሉ እናደርጋለን ብለው መለሱ፤ሙሴም የሕዝቡን ቃል ወደ እግዚአብሔር አደረሰ” ዘጸ 19፥8
ቅዱስ ጳውሎስ በኤፌሶን መልእክቱ “በሰላም ማሰሪያ የመንፈስን አንድነት ለመጠበቅ ትጉ” ብሎናል። አንድነት የሰላም መገኛ ነውና አንድነት ሲኖር ሰላም ይኖራል። የተወደዳችሁ ልጆቻችን አንድነት ከላይ የተጠቀሱትን እና ሌሎችን ፍሬዎች የተሸከመ ትልቅ ዛፍ ስለሆነ ፍሬዎቹን ማግኘትና መብላት የምንፈልግ ሁሉ ዛፉን መንከባከብና መጠበቅ አለብን።

ሰላመ እግዚአብሔር ከሁላችን ጋር ይሁን ።

Map of በኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክ ርዕሰ አድባራት ዱባይ ሻርጃ አጅማን ሰአሊተ ምሕረት ቅድስት ማርያም ቤ/ክ ቤዛ ብዙኃን ሰ/ት/ቤት

OTHER PLACES NEAR በኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክ ርዕሰ አድባራት ዱባይ ሻርጃ አጅማን ሰአሊተ ምሕረት ቅድስት ማርያም ቤ/ክ ቤዛ ብዙኃን ሰ/ት/ቤት